ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ፈጣሪ እግዚአብሔር
ወደዚህ ምድር በኢየሱስ ስም መጥቶ አዲስ ኪዳንን አቋቋመ።
በአዲሱ ኪዳን አማካኝነት፣ በኃጢአትና በሞት እየተሰቃዩ
ያሉት የእግዚአብሔር ልጆች፣ የኃጢአት ይቅርታና
የዘላለም ሕይወት ማግኘት ይችላሉ።
ለሦስት ዓመታት ያህል፣ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ
አዲሱን ኪዳን በመጠበቅ ረገድ ምሳሌ ትቷል።
እኔ እንዳደረግሁላችሁ እናንተም እንደዚሁ እንድታደርጉ
ምሳሌ ትቼላችኋለሁ። ዮሐ 13፥15
የኢየሱስን ቃል በመከተል ደቀ መዛሙርቱ
አዲሱን ቃል ኪዳን ሰበኩ።
በአዲሱ ኪዳን የኃጢአት ይቅርታ ማግኘት
የምንችልበት የአምልኮ ሥርዓት አለ።
ወንድ በአምልኮ ሂደት ውስጥ ራሱን ከሸፈነ፣ እግዚአብሔር ያዋርዳል።
ሴት ራሷን ካልሸፈነች የእርሷን ራስ ታዋርዳለች፤ (1 ቆሮንቶስ 11፥4-5)
በክርስቶስ በተቋቋመ አዲስ ኪዳን በምትከተል ቤተ ክርስቲያን
ሴት በአምልኮ ጊዜ እራሷን በመሸፈኛ ትሸፍናለች፣
ወንድ ግን አይሸፍንም።
ሆኖም፣ ከኢየሱስ ዕርገት በኋላ፣ አንዳንድ ሴቶች በአምልኮ
ውስጥ መሸፈኛ ማድረግ እንደሌለባቸው አጥብቀው ይገልፃሉ።
በዚህ ምክንያት ሐዋርያው ጳውሎስ ረጅም ፀጉር በሰው
ልጅ ተፈጥሮ ለሴት እንደሚያምር በመግለጽ መሸፈኛ
እንዲለብሱ አሳስቧቸዋል።
እስቲ እናንተ ፍረዱ፤ ሴት ራሷን ሳትሸፍን ወደ
እግዚአብሔር መጸለይ ይገባታልን?
ወንድ ጠጕሩን ቢያስረዝም ነውር እንደሚሆንበት
ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን?
ሴት ግን ጠጕሯን ብታስረዝም ክብሯ አይደለምን?
ረዥም ጠጕር የተሰጣት መጐናጸፊያ እንዲሆናት ነውና።
እንግዲህ ማንም በዚህ ጕዳይ ላይ መከራከር ቢፈልግ፣
እኛም ሆንን የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ከዚህ
የተለየ ልማድ የለንም።
1 ቆሮንቶስ 11፡13–16
መጽሐፍ ቅዱስ አንዲት ሴት በአምልኮ ጊዜ ራሷን
በመሸፈኛ እንድትሸፍን በግልፅ ይናገራል።
ለሴት በአምልኮ ጊዜ መሸፈኛ የመልበስ ተግባር ኢየሱስ
ያስተማረውና ሐዋርያው ጳውሎስ የሰበከው
የአዲስ ኪዳን ሥርዓች አንዱ ነው።
የመሸፈኛ ሥርዓት መከተል የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።
119 የቡንዳንግ ፖ.ሳ.ቁ፣ ቡንዳንግ-ጉ፣ ሲኦንግናም-ሲ፣ ግዮንጊ-ዶ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ስልክ 031-738-5999 ፋክስ 031-738-5998
ዋና ምስሪያ ቤት፡ 50፣ ሱኒ_ሮ ፣ ቡንዳኔግ_ጉ፣ ሲዮንግያም_ሲ፣ ግዋንጊዶ_ሲ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ዋና ቤተ ክርስቲያን፡ 35፣ ፓንግዮዬክ_ ሮ ቡንዳንግ _ጉ፣ ሶንግያም ሲ፣ ጊዮኔጊ_ዱ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
World Mission Society Church of God ሁሉም መብቶች የተጠብቁ ናቸው። ግላዊ ደኅንነት