ሳልሞን በባሕር ውስጥ ይኖራል ከዚያም ወደ ትውልድ ቦታው ይመለሳል እና ለመራባት ይሞክራል። በዚያ ሂደት ውስጥ፣ አንድ ሳልሞን ሳይበላ የተከማቸውን ጉልበቱን በመጠቀም ሕመሙን እንደሚቋቋም ሁሉ፣ እኛም በዚህ ዓለም የተማርናቸውን መጥፎ ልማዶችና ባሕርያት ሁሉ በማስወገድ እንደገና የመወለድን ሥቃይ ማሸነፍ እና አባትና እናታችን ወደሚኖሩበት ዘላለማዊ ሰማያዊ ቤታችን ለመመለስ መጣር አለብን።
በዚህ ጊዜ፣ ሁሉም ብሔራት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተነገረው ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት እናት ክንዶች ሲበሩ፣ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን አባላት ሁልጊዜ “የእናት ፍቅር ቃላትን” እንደ እርሷ ትምህርት ይለማመዳሉ፣ የኢየሩሳሌምን ሰማያዊት እናት ክብር በመልካም ሥራቸው ለዓለም ሁሉ ይገልጣሉ።
መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12:2
“ብርሃንሽ መጥቷልና ተነሺ አብሪ፤ የ እግዚአብሔር ም ክብር ወጥቶልሻል። እነሆ፤ ጨለማ ምድርን፣ ድቅድቅ ጨለማም ሕዝቦችን ይሸፍናል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ወጥቶልሻል፤ ክብሩንም ይገልጥልሻል። ሕዝቦች ወደ ብርሃንሽ፣ ነገሥታትም ወደ ንጋትሽ ጸዳል ይመጣሉ። ኢሳይያስ 60:1–3
119 የቡንዳንግ ፖ.ሳ.ቁ፣ ቡንዳንግ-ጉ፣ ሲኦንግናም-ሲ፣ ግዮንጊ-ዶ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ስልክ 031-738-5999 ፋክስ 031-738-5998
ዋና ምስሪያ ቤት፡ 50፣ ሱኒ_ሮ ፣ ቡንዳኔግ_ጉ፣ ሲዮንግያም_ሲ፣ ግዋንጊዶ_ሲ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ዋና ቤተ ክርስቲያን፡ 35፣ ፓንግዮዬክ_ ሮ ቡንዳንግ _ጉ፣ ሶንግያም ሲ፣ ጊዮኔጊ_ዱ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
World Mission Society Church of God ሁሉም መብቶች የተጠብቁ ናቸው። ግላዊ ደኅንነት